SnatchApp ግለሰቦች እና ድርጅቶች በመላው ዓለም ኢንተርኔትን በመጠቀም ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ግንኙነት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነጻ የመልዕክት እና የመደዋወያ አፕሊኬሽን ነው።
ከመነሻው እስከ መድረሻው ድረስ የተመሰጠሩ (ኢንክሪፕት የተደረጉ) መልዕክቶችን፣ ፈጣን የድምጽ መልዕክቶችን፣ ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን፣ ሰነዶችን፣ የስሜት ገላጭ ምስሎችን፣ የስልክ ጥሪዎችን እና የቪዲዮ ጥሪዎችን ለመላክ እና ለመቀበል ቀላል የሆነ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ነው።
በ SnatchApp ውስጥ ግባችን እጅግ ቀላል ነው፥ ሰዎችን ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ግንኙነታቸው ሳይቋረጥ እንዲቀጥሉ ማገዝ። ይህን ዓላማ ፍሬያማ ለማድረግም ነፃ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ለአጠቃቀም ምቹ እና በሁሉም ቦታ የሚገኝ ምርት ፈጥረናል። መልዕክቶችዎን ከሁሉም መሳሪያዎችዎ በአንድ ጊዜ ማየትም ይችላሉ።
በተጨማሪም SnatchApp ቻትቦትስን (chatbots) በማካተት በመላው ዓለም በሚገኙ በሁሉም ሀገሮች ውስጥ ማለት ይቻላል ግላዊነታቸው በተጠበቀ መልኩ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የመልዕክቶች ልውውጥን ያስችላል።
SnatchApp በ53 የተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል።
SNATCHAPP ን መጠቀም ለምን ተመራጭ ይሆናል?
• የተመሰጠሩ ነፃ የድምፅ እና ቪድዮ ጥሪዎች: ምንም እንኳን ወዳጅ ዘመዶችዎ በሌላ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ቢሆኑም ኮምፒተርዎን ወይም ስማርትፎን በመጠቀም በነፃ የልብዎትን ይጨዋወቱ። SnatchApp የስልክ እቅድ የድምፅ ደቂቃዎችዎን ከመጠቀም ይልቅ በስልክዎትን ኢንተርኔት (4G/3G/2G/EDGE ወይም Wi-Fi እንደሁኔታው) የሚጠቀም ስለሆነ፣ ለእያንዳንዱ መልዕክት ወይም የስልክ ጥሪ መክፈል አይጠበቅብዎትም። (ማስታወሻ፥ በ Wi-Fi የሚደረጉ ጥሪዎች ነጻ ናቸው። መደበኛ የዳታ ክፍያዎች ግን ሊተገበሩ ይችላሉ)።
• ምስጢራዊነቱ የተጠበቀ የመልእክት መላላኪያ እና የስም ዝርዝሮች፥ ሁሉም መልዕክቶች እና ጥሪዎች ከመነሻ እስከ መድረሻ ድረስ በምስጠራ ይጠበቃሉ። ከትክክለኛው ሰው ጋር እየተነጋገሩ መሆንዎትን ለማረጋጥ፣ በስልክዎት ላይ ካሉት የስም ዝርዝሮች ጋር ከመነሻ እስከ መድረሻ ድረስ ያለውን ምስጠራ ደህንነት መጠበቁን ያረጋግጡ።
• የቡድን ውይይት እና ጥሪዎች፥ ለእርስዎ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ሰዎች ጋር በጋራ ለመጨዋወት SnatchAppን ይጠቀሙ። የቡድን የስልክ ጥሪዎችን ያድርጉ። ትልልቅ ቪዲዮዎችን፣ ጽሁፎችን፣ ማንኛውንም አይነት ሰነድ፣ ፎቶግራፎችን፣ ድምጽን፣ የአካባቢ መልዕክቶችን እና ሌሎች ነገሮችንም በቡድን በማጋራት ይደሰቱ።
• SnatchApp ድህረ-ገጽ፥ በተጨማሪም SnatchApp በድህረ-ገጽ ብሮውዘርዎ ላይም ይገኛል። https://web.snatchapp.me
• ለቦትስ (Bots) ተመራጭ ጣቢያ፥ - ቻትቦትስን ን ለመፍጠር እና ተግባራዊ ለማድረግ እያሰቡ ከሆነ፣ የ SnatchApp ግላዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አፕሊኬሽንን በመጠቀም መተግበር፣ መሞከር እና ከአውቶማቲክ ሲስተሙ ጋር መስተጋብር መፍጠር ይችላሉ።
• በማንኛውም ሰዓት ያሉበትን ቦታ ጠቋሚ፥ ለሌሎች ሰዎች ያሉበትን ቦታ ከመናገር ይልቅ፣ ካርታዎችን ከማንኛውም ውይይት ጋር ለማጣመር በማንኛውም ሰዓት ያሉበትን ቦታ ጠቋሚ ማጋሪያን ይጠቀሙ።
• ድምጽዎትን ይቀይሩ፥ በነገሮች ላይ ቅመም ጣል አድርገው የሚወዷቸውን ሰዎች ሊያስደንቁ ይፈልጋሉ? SnatchApp የድምፅዎትን ቃና ለመቀየር ያስችልዎታል። የቀየሩትን ድምጽዎትን እያዳመጡ ይዝናኑ!
ደህንነት፥
• ደህንነቱ የተጠበቀ፥ በ SnatchApp ላይ ያሉ ሁሉም መልዕክቶች የ 256-ቢት ተመጣጣኝ AES ምስጠራ፣ 2048-ቢት RSA ምስጠራ እና ለእያንዳንዱ ውይይት ደህንነቱ የተጠበቀ የቁልፍ ልውውጥ ጥምረቶችን በመጠቀም የተመሰጠሩ ናቸው። በ SnatchApp በኩል የተላኩ መልዕክቶችን ማንበብ በፍጹም አንችልም። በ SnatchApp በኩል የሚልኳቸውን መልዕክቶች እና ማንኛውንም አይነት ሰነዶች ልናገኛቸው አንችልም።
• መሉ ለሙሉ ማስወገጃ፥ ከኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎት ላይ ሁሉም የመልዕክቶች፣ የምስሎች እና የቪዲዮዎች ይዘቶች በሙሉ እንዳይመለሱ ሆነው ሊሰረዙ ይችላሉ።
• የሚጠፉ መልዕክቶችን እንዲታዩ/እንዳይታዩ ማድረግ፥ በመሰረታዊ ቅንብር (ዲፎልት) ላይ፣ በውይይት ውስጥ የተላኩ ሁሉም መልዕክቶች ከታዩ በኋላ ወዲያው ይጠፋሉ።
• የሰዓት ቆጣሪውን ማስተካከል፥ በሁሉም መልዕክቶችዎ የመልእክቶቹን መቆያ ጊዜ ይቀያይሩ።
• ያለስጋት ይገናኙ፥ የአድራሻ ደብተርዎ ሁልጊዜ ግላዊ ሲሆን በምንም አይነት በእኛ ሰርቨሮች ላይ የሚቀመጥ አይሆንም። የጓደኛ ፈላጊ ከ Google, Yahoo, Outlook, ኢሜል፣ ስልክ ጋር ተጣምሯል።
• 100% ነፃ እና ምንም አይነት ማስታወቂያ የሌለበት፥ SnatchApp ነፃ ሲሆን ወደፊትም ነጻ እንደሆነ እስከመጨረሻው ይቆያል።
------------------------
ስለ SnatchApp ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ ኦፊሴላዊ ድህረ-ገጻችንን ይጎብኙ፥
http://snatchapp.me