ይህ የRaw ምስል ቅጥያ ስሪት በርካታ የሳንካዎች ማስተካከያ ከማድረግ በተጨማሪ የCR3 ፋይሎች ድጋፍ አካቷል!
ለRaw ምስል ቅጥያ ፍላጎት ስላሳዩ እናመሰግናለን። በመሳሪያዎችዎ ላይ ለመጫን ቅጥያውንሊ ያገኙት ይችላሉ፣ ነገር ግን ቅጥያውን ለመጫን Windows 10 ሜይ 2019 ዝማኔ (ስሪት ቁጥር 1903) ያስፈልጋል።
ጥሬ ምስል ቅጥያ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ በሚገኙ ዲጂታል ካሜራዎች የተቀረጹ ምስሎች በraw ፋይል ቅርጸታቸው ነባር ዕይታ ድጋፍ ያክላል። ጥቅሉን በመጫን፣ የሚደገፉ raw ፋይል ቅርጸቶችን ጥፍር አከሎችና ዲበ ውሂብ በቀጥታ Windows ፋይል ኤክስፕሎረር ውስጥ እንዲመለከቱ ወይም ምስሎችን በፎቶዎች መተግበሪያ ውስጥ እንዲያዩ ያስችልዎታል። አሁን ያለው የቅጥያ ስሪት በጣም ብዙ የካሜራ ዝርዝሮች ይደግፋል፣ ነገር ግን እንደ .GPR የመሳሰሉት የተወሰኑ Raw ቅርጸቶች በአሁኑ ጊዜ አይደገፉም።
ይህ ጥቅል ዕውን እንዲሆን ያስቻለውን libraw ክፍት ምንጭ ፕሮጀክት (http://www.libraw.org) ማመስገን እንፈልጋለን። ለሚደገፉ የካሜራዎች ዝርዝር https://www.libraw.org/supported-cameras ላይ ይመልከቱ። Libraw ላይብራሪ COMMON DEVELOPMENT AND DISTRIBUTION LICENSE ስሪት 1.0 (CDDL-1.0) መሰረት ያደረገ ነው
እባክዎ ያስታውሱ – በዚህ ቅጥያ የሚቀርበው Raw ኮዴክ ለመስራት በWindows ላይ ለውጦች እንዲኖሩ ይፈልጋል። Windows 10 ሜይ 2019 ዝማኔ (ስሪት ቁጥር 1903) ወይም ከዚያ በኋላ ይፈልጋል። ቅጥያውን መጫን ካልቻሉ፣ መሳሪያዎ ቅጥያው እንዲሰራ የሚፈልገውን ዝቅተኛ የWindows ግንባታ ቁጥር የማያሟላ Windows ይጠቀማል ማለት ነው። ቅጥያውን ለመጫን እባክዎ መሳሪያዎን ወደ የቅርብ ጊዜው Windows ስሪት ለማሻሻል ያስቡበት።
እባክዎ ልብ ይበሉ – ቅጥያው መተግበሪያ አይደለም – በቀጥታ መስተጋብር ሊፈጥሩበት አይችሉም። ፋይል ኤክስፕሎረር እና ፎቶዎች ጨምሮ የWindows መተግበሪያዎች ጥሬ ምስሎችን ምስጠራ ለመፍታት የሚጠቀሙበት OS ኮዴክ ተሰኪ ይጭኛል። ቅጥያውን ከጫኑ በኋላ ከሚደገፉ ካሜራዎች የጥሬ ምስሎችዎን ጥፍር አከሎችን ለማየት ፋይል ኤክስፕሎረር ወይም ጥሬ ምስሎችን ለማየት ፎቶዎች መተግበሪያን ይጠቀሙ።